Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 5 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
"ኃጢዓትን የሠራ ከዚያም ተነስቶ ዉዱእ አድርጎ የሚሰግድ ከዚያም ለኃጢዓቱ ከአሏህ ምህረት የሚጠይቅ አንድም ሰው የለም፤ አላህ ለርሱ የሚምረው ቢሆን እንጂ።› ቀጥለውም ይህቺን አንቀፅ አነበቡ {ለእነዚያም መጥፎ ስራን በሰሩ ወይም ነፍሶቻቸውን በበደሉ ጊዜ አላህን የሚያስታውሱና ለሀጢዐቶቻቸው ምህረትን የሚለምኑ ለሆኑት} [ኣሊ ዒምራን:135] '"
ሶሒሕ ነው። አቡዳወድ፣ ቲርሚዚ፣ ነሳኢ በኩብራ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።
"እኔና ዱንያ ምን አገናኘን? እኔ ዱንያ ውስጥ ዛፍ ስር ተጠልሎ ከዚያም ትቷት እንደሄደ ተጓዥ አምሳያ እንጂ ሌላ አይደለሁም።"»
ሶሒሕ ነው። ቲርሚዚና ኢብኑማጀህ ዘግበውታል።
"የሰው ልጅ እንደሆዱ መጥፎን ቋት አልሞላም። የአደም ልጅ ወገቡን ቀና የሚያደርጉለት ጥቂት ጉርሻዎች ይበቁታል። (መጥገቡ) የማይቀር ከሆነ (የሆዱን) ሲሶውን ለምግቡ፣ ሲሶውን ለመጠጡ፣ ሲሶውን ለትንፋሹ ያድርግ።"
ሶሒሕ ነው። ኢማም አሕመድ፣ ቲርሚዚይ፣ ነሳኢይ እና ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል
"ዕውቀትን ዑለሞችን ልትፎካከሩበት (በሊቃውንት ፊት ለመታየት)፣ ቂሎችን ልትሟገቱበት፣ በመድረኮች ላይ ቅድሚያ እንድትመረጡበት በማለም እንዳትቀስሙ። ይህን የፈፀመ (ለርሱ) እሳት አለው እሳት አለው።"
ሶሒሕ ነው። ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል።
የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በአብዛኛው ሰዎችን ጀነት ስለሚያስገባው ነገር ተጠየቁ፤ እሳቸውም "አላህን መፍራት እና መልካም ስነምግባር ነው።" አሉ። በአብዛኛው ሰዎችን እሳት ስለሚያስገባቸው ነገርም ተጠየቁ። እሳቸውም "ምላስና ብልት ነው።" አሉ።
ሐሰኑን ሶሒሕ ነው። ቲርሚዚ፣ ኢብኑ ማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።