Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 106 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
"ስራዎች (ተቀባይነታቸው የሚለካው) በኒያ ብቻ ነው። ማንኛውም ሰው የሚመነዳውም ባለመው ኒያ ልክ ብቻ ነው። ስደቱ ወደ አላህና ወደ መልዕክተኛው ብሎ የሆነ ሰው (ምንዳውም) ለአላህና ለመልእክተኛው ሆኖለታል፤ የዱንያን ጥቅም ለማግኘት ወይም ሴትን ለማግባት ብሎ የተሰደደ ሰውም የስደቱ (ምንዳ) ለተሰደደለት ጉዳይ ነው።"»
ሶሒሕ ነው። ሁለቱ የሐዲሥ ሊቃውንት ኢማሞች (መሪዎች) አቡ ዐብዲላህ ሙሐመድ ቢን ኢስማዒል ቢን ኢብራሂም ቢን አል-ሙጊራህ ቢን በርዲዝበህ አል-ቡኻሪ እና አቡል ሑሰይን ሙስሊም ቢን አል-ሐጃጅ ቢን ሙስሊም አል-ቁሸይሪይ አን-ነይሳቡሪይ ከተጻፉት መጻሕፍት ሁሉ ይበልጥ ትክክለኛ በሆኑት በሁለቱ ሰሒሕ መጻሕፍቶቻቸው ውስጥ ዘግበውታል።
"ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እጅግ አብዝተው ያደርጉት የነበረው ዱዓ 'አልላሁመ ረበና አቲና ፊ ዱንያ ሐሰነተን ወፊል አኺረቲ ሐሰነተን ወቂና ዓዛበን-ናር' የሚለውን ነበር።" (ትርጉሙም: ጌታችን አላህ ሆይ! በዱንያ መልካሙን ስጠን፤ በመጨረሻው ዓለምም መልካሙን ስጠን። ከእሳት ቅጣትም ጠብቀን።) ማለት ነው።
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ጌታውን የሚያወሳና የማያወሳ ሰው ምሳሌ እንደ ህያውና እንደ ሞተ ሰው ምሳሌ ነው።"» በሙስሊም ዘገባ ደሞ "በውስጡ አላህ የሚወሳበት ቤትና አላህ የማይወሳበት ቤት ምሳሌ እንደ ህያውና እንደሞተ ሰው ምሳሌ ነው።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"አንዳችሁ በአላህ ላይ ያለውን እሳቤ ሳያሳምር እንዳይሞት።"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
«የአላህን መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ስለድንገተኛ እይታ ጠየቅኳቸው። እርሳቸውም አይኔን እንዳዞር አዘዙኝ።»
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"ዱንያ ጣፋጭና አረንጓዴ (ለምለም) ናት። አላህም እንዴት እንደምትሰሩ ሊያያችሁ በውስጧ ምትኮች አድርጓችኋል። ዱንያንም ተጠንቀቁ! ሴቶችንም ተጠንቀቁ! የበኒ ኢስራኢሎች የመጀመሪያ ፈተና የተከሰተው በሴቶች ነበርና።"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"የአደም ልጆች ቀልቦች ሁሉ ከአርራሕማን ጣቶች በሁለቱ ጣቶች መካከል ናቸው። (እርሱ ዘንድ ሁሉም ቀልቦች) እንደ አንድ ቀልብ ናቸው። እንደፈለገ ይገለባብጣቸዋል።" ቀጥለውም የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ አሉ "ቀልቦችን አዘዋዋሪ የሆንከው አላህ ሆይ! ቀልባችንን በአምልኮህ ላይ አዙረው።"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"ከኔ በኋላ ለወንዶች ከሴት የበለጠ እጅግ ጎጂ ፈተና አልተውኩም።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።