Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 106 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
"በአሏህ ሳያጋራ አሏህን የተገናኘ ጀነት ገብቷል፤ እያጋራበት አሏህን የተገናኘ ደግሞ እሳት ገብቷል።"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"አንድም መከራ አጋጥሞት አላህ እንዳዘዘው ‹{ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን} [አልበቀራ:156] አልላሁመእጁርኒ ፊ ሙሲበቲ፣ ወአኽሊፍ ሊ ኸይረን ሚንሃ› የሚል ሙስሊም የለም አላህ ከዛ የተሻለ ነገር ቢተካለት እንጂ።"» ኡሙ ሰለማ እንዲህ አለች: "አቡ ሰለማ የሞተ ጊዜ እንዲህ አልኩኝ: ከአቡ ሰለማ የተሻለ ሙስሊም ከቶ ማን አለና?! ወደ አላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- በቅድሚያ የተሰደደ ቤተሰብ ነው። ከዚያም ይህንን ዱዓ አልኩኝ። አላህም ለኔ የአላህን መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ተካልኝ።" ትርጉሙም ({እኛ ለአላህ ነን እኛም ወደርሱ ተመላሾች ነን።} [አልበቀራ:156] አላህ ሆይ በመከራዬ ምንዳን ስጠኝ። ከደረሰበኝ መከራ የተሻለንም ተካልኝ።) ማለት ነው።
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"አላህ ዘንድ ተወዳጅ የሆኑ ንግግሮች አራት ናቸው። 'ሱብሓነላህ' (አላህ ሆይ! ጥራት ተገባህ) 'አልሐምዱ ሊላህ' (ምስጋና ለአላህ የተገባ ነው።) 'ላኢላሃ ኢለላህ' (ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም) 'አሏሁ አክበር' (አላህ ታላቅ ነው።) በማንኛቸውም ብትጀምር አይጎዳህም።"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"እናንተ ሰዎች ሆይ! ወደ አላህ ተመለሱ (ተውበት አድርጉ)፤ እኔ በቀን መቶ ጊዜ ወደርሱ እመለሳለሁ (ተውበት አደርጋለሁ።)"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"አልላሁመ ለከ አስለምቱ፣ ወቢከ አመንቱ፣ ወዐለይከ ተወከልቱ፣ ወኢለይከ አነብቱ፣ ወቢከ ኻሶምቱ፤ አልላሁመ ኢኒ አዑዙ ቢዒዘቲከ፣ ላኢላሃ ኢላ አንተ አንቱዲለኒ፣ አንተልሐይዩ ለዚ ላየሙት፣ ወልጂኑ ወልኢንሱ የሙቱን" ትርጉሙም "አላህ ሆይ! ላንተ እጅ ሰጥቻለሁ፤ ባንተም አምኛለሁ፤ ባንተም ላይ ተመክቻለሁ፤ ወዳንተም ተመልሻለሁ፤ ባንተ መንገድም ተሟግቻለሁ፤ አላህ ሆይ! እኔ እንዳታጠመኝ በልቅናህ እጠበቃለሁ፤ ካንተ በቀርም በእውነት የሚመለክ የለም። የማይሞት ህያው አንተው ነህ። ጋኔንም ሰውም ይሞታሉ።" ማለት ነው።
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል ቃሉ የሙስሊም ዘገባ ነው፤ ቡኻሪ ደግሞ በአጭሩ ዘግበውታል
«ጀነት ውስጥ የአንዳችሁ ትንሹ ደረጃ አላህ ለርሱ "ተመኝ" ይለዋል። እርሱም ደጋግሞ ይመኛል። አላህም ለርሱ "ተመኘህን?" ይለዋል። እርሱም "አዎን" ይላል። አላህም ይለዋል: "ላንተ የተመኘኸውንም ከርሱም ጋር የርሱን አምሳያ ሌላም ይሰጥሃል።"»
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
«የአላህን መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ስለበጎ ተግባርና ስለወንጀል ጠየቅኳቸው። እርሳቸውም " በጎ ተግባር ማለት መልካም ስነምግባር ነው። ወንጀል ማለት በልብህ ውስጥ የተጣረጠርከውና (የተመላለሰ) ሰዎች ማወቃቸውን የጠላኸው ነገር ነው።" አሉኝ።»
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"አንድ ባሪያ ወደ ጌታው እጅግ ቅርብ የሚሆነው ሱጁድ ላይ ሳለ ነው። (ስለዚህም) ዱዓእን አብዙ!"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።