Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 106 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
"ሁለት ሙስሊሞች በሰይፋቸው (ሊጋደሉ) የተገናኙ ጊዜ ገዳዩም ሆነ ተገዳዩ እሳት ውስጥ ናቸው። " እኔም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ይህ ገዳይ ሆኖ (እሳት መግባቱ መልካም) ተገዳዩ (እሳት የሚገባው) በምን ጥፋቱ ነው?" አልኩ። እርሳቸውም "እሱ ባልደረባውን ለመግደል ጉጉ ስለነበር ነው።" አሉ።
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡ ' እኔ በሽርክና ከመጋራት ከተብቃቁ ሁሉ እጅግ የተብቃቃሁ ነኝ። ከኔ ጋር ሌላን አጋርቶ ስራን የሰራ እሱንም ማጋራቱንም እተወዋለሁ።'"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"ንፅህና የኢማን ግማሽ ነው 'አልሐምዱ ሊላህ' (ምስጋና ለአላህ የተገባ ነው) የሚለው ሚዛን ይሞላል፤ 'ሱብሐነላህ ወል'ሐምዱ ሊላህ' (አላህ ጥራት የተገባው ነው፤ ምስጋናም ሁሉ ለአላህ ነው) የሚለው በሰማያትና በምድር መካከል ያለውን ይሞላሉ ወይም ይሞላል ፤ ሰላት ብርሃን ነው፣ ምጽዋት ማስረጃ ነው፣ ትዕግስት ወገግታ (አንፀባራቂ ብርሃን) ነው፣ ቁርኣን ላንተ ወይም በአንተ ላይ ማስረጃ ነው። ሁሉም ሰው በማለዳ ወጥቶ ነፍሱን ይሸጣል። ወይ ከጥፋት ነፃ ያወጣታል ወይም ወደ ጥፋት ይጥላታል። "
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"እናንተ የምትፈልጉትን ምግብና መጠጥ እየተመገባችሁ አይደልንዴ? ነቢያችሁን -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሆዳቸውን የሚሞሉበት የሆነ የወረደ ተምርን እንኳ ሳያገኙ ቀርተው ተመልክቻቸዋለሁ።"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"(ላኢላሃ ኢለሏህ ወሕደሁ ላሸሪከ ለህ ለሁልሙልኩ ወለሁልሐምዱ ወሁወ ዐላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር) የሚለውን ውዳሴ በቀን ውስጥ መቶ ጊዜ ያለ ሰው ለርሱ አስር ባሪያዎችን ነፃ እንዳወጣ ይቆጠርለታል፤ መቶ ምንዳም ለርሱ ይጻፍለታል፤ መቶ ኃጢአቶችም ከርሱ ላይ ይሰረዛሉ፤ ቀኑንም እስኪያመሽ ድረስም ለርሱ ከሸይጧን መጠበቂያ ትሆንለታለች፤ እርሱ ከሰራው የበለጠ አብዝቶ የሰራ ሰው ካልሆነ በቀር አንድም ሰው ከርሱ የበለጠም አልሰራም።" ትርጉሙም (ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም። ብቸኛና አጋር የሌለውም ነው። ንግስና የርሱ ነው። ምስጋናም ለርሱ ነው። እርሱም በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነው።)
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"አንዱ በአንዱ ላይ በማይፎክርና አንዱ በአንዱ ላይ ወሰን በማይተላለፍበት ልክ እንድትተናነሱ አላህ ወደኔ ራዕይ አውርዷል።"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"አላህ ወደ ቅርፃችሁና ገንዘቦቻችሁ አይመለከትም ነገር ግን ወደ ልቦቻችሁና ስራዎቻችሁ ይመለከታል።"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"ከናንተ በፊት ከነበሩት ህዝቦች መካከል አንድ የቆሰለ ሰውዬ ነበር። ትእግስት በማጣቱም ቢላ አንስቶ እጁን ቆረጠ። እስኪሞት ድረስም ደሙ አልተቋረጠም። አላህም እንዲህ አለ: 'ባሪያዬ ነፍሱን በማውጣት ተቻኮለኝ። በርሱ ላይም ጀነትን እርም አድርጌበታለሁ።' "
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።