Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 21 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
«የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "ያ ሙቀሊበል ቁሉብ ሠቢት ቀልቢ ዐላ ዲኒክ" (አንተ ልቦናን ገለባባጭ የሆንክ ጌታ ሆይ! ልቤን በሃይማኖትህ ላይ አፅናት) ማለትን ያበዙ ነበር። እኔም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! በርሶና ይዘውት በመጡት ሃይማኖት አምነናል። በኛ ላይ የሚፈሩልን ጉዳይ አለ ማለት ነው?" አልኳቸው። እርሳቸውም "አዎን ልቦች በአላህ ሁለት ጣቶች መካከል ናቸው። እንደፈለገው ይገለባብጣታል።" አሉኝ።»
ሶሒሕ ነው። ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።
"አላህ ሆይ! እኔ በእዳ ከመሸነፍ፣ በጠላት ከመሸነፍና የጠላቶች ደስታ ምንጭ ከመሆን ባንተ እጠበቃለሁ።"
ሶሒሕ ነው። ነሳኢና አሕመድ ዘግበውታል።
«የአላህ መልክተኛ ሆይ! አላህን የምጠይቀው አንዳች ነገር አስተምሩኝ? አልኳቸው። እርሳቸውም "አላህ ደህና እንዲያደርግህ ጠይቀው" አሉኝ። ቀናትን ቆይቼ ከዚያም መጣሁና የአላህ መልክተኛ ሆይ! አላህን ዐዘ ወጀል የምጠይቀው አንዳች ነገር አስተምሩኝ? አልኳቸው። እርሳቸውም ለኔ "ዐባስ ሆይ! የአላህ መልክተኛ አጎት ሆይ! አላህን በዱንያና በመጪው አለም ደህንነትን ጠይቀው።" አሉኝ።»
በሌላ ሰነድ ታግዞ ሶሒሕ ነው። ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።
"የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ጠቅለል ያሉ ዱዓዎችን ማድረግ ይወዱ ነበር። ከዚህ ውጪ ያለውንም ይተዉ ነበር።"
ሶሒሕ ነው። አቡዳውድና አሕመድ ዘግበውታል።
"አማኝ የሆነ ወንድና ሴት በርሱ ላይ ምንም ወንጀል የሌለበት ሆኖ አላህን እስኪገናኝ ድረስ በነፍሱ፣ በልጁና በገንዘቡ ላይ መከራ ከመከሰት አይወገድም።"»
ሐሰን ነው። ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።