Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 2 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
"ሰዎች በመክሰሳቸው ብቻ ቢሰጣቸው ኖሮ ሰዎች የሌሎችን ገንዘብና ደም (ለመውሰድ) ይከሱ ነበር። ነገር ግን ማስረጃ በከሳሽ ላይ፣ መሀላ ደግሞ ክሱን ባወገዘ ሰው ላይ ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ተደረገ።"
ሶሒሕ ነው። በይሀቂይ ዘግበውታል
"የሙስሊምን ሰው ገንዘብ ለመውሰድ እየዋሸ የማለ ሰው አላህ በርሱ ላይ የተቆጣበት ሆኖ ይገናኛል።" አሽዓሥም እንዲህ አለ: "በአላህ እምላለሁ! ይህንን የተናገሩት በኔ ምክንያት ነበር። በኔና በአንድ አይሁድ መካከል የመሬት ውል ነበረንና ካደኝ። ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ዘንድም ለፍርድ አቆምኩት። የአላህ መልክተኛም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- "ማስረጃ አለህን?" አሉኝ። እኔም "የለኝም።" አልኩኝ። ከዛም ለአይሁዱ "ማል።" አሉት። እኔም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እንዲህ ከሆነማ ምሎ ገንዘቤን ይወስዳል።" አልኳቸው። አላህም {እነዚያ በአላህ ቃል ኪዳንና በመሐላዎቻቸው ጥቂትን ዋጋ የሚለውጡ ... } ሙሉ አንቀፁን አወረደ።"»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።