Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 5 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
«ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከመፀዳጃ ቤት የወጡ ጊዜ "ጉፍራነክ" ይሉ ነበር።» (ትርጉሙም "ምህረትህን እለምንሃለሁ" ማለት ነው።)
ሶሒሕ ነው። አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።
'ሲዋክ አፍን የሚያጠራ (የሚያፀዳ)፤ የአሏህንም ውዴታ የሚያስገኝ ነው።'"
ሶሒሕ ነው። ነሳኢና አሕመድ ዘግበውታል።
"የዐብዱረሕማን ቢን ዐውፍ ባለቤት የነበረችው ኡሙ ሐቢባ ቢንት ጀሕሽ የአላህ መልክተኛን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ስለምታየው ደም ስሞታ አቀረበች። እርሳቸውም 'የወር አበባሽ የሚያግድሽ ቀናት ያክል (ሳትሰግጂ ሳትፆሚ) ቆዪ ከዚያም ታጠቢ።' አሏት። እርሷም ለሁሉም ሶላት ትታጠብ ነበር።"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
" 'እኔ የበሽታ ደም ይፈሰኛልና አልፀዳም። ሶላት ልተውን?' እርሳቸውም 'በፍፁም! ይህ የደም ስር መቆረጥ ነው። ባይሆን የወር አበባ ስታይበት በነበርሽው የቀናት ልክ ሶላትን ተይ! ከዚያም ታጠቢና ስገጂ።' አሏት።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከጀናባ በሚታጠቡ ጊዜ ሁለት እጃቸውን ይታጠቡና ለሶላት የሚያደርጉትን አምሳያ ዉዱእ ያደርጋሉ። ከዚያም (ሙሉ ገላቸውን) ይታጠቡ ነበር። ከዚያም በእጃቸው ፀጉራቸውን ይፈለፍላሉ። (የፀጉራቸው) ቆዳ በውሃ መራሱን እስከሚያስቡ ድረስም እየፈለፈሉ በጭንቅላታቸው ላይ ሶስት ጊዜ ውሃን ያፈሳሉ። ከዚያም ቀሪ ሰውነታቸውን ያጥባሉ።" ዓኢሻ እንዲህም ብላለች: "እኔና የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከአንድ እቃ ሁለታችንም እየዘገንን እንታጠብ ነበር።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪ ዘግበውታል።