Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 38 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
"ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መፀዳጃ ቤት የገቡ ጊዜ 'አልላሁመ ኢንኒ አዑዙ ቢከ ሚነል ኹብሢ ወልኸባኢሥ' ይሉ ነበር።" ትርጉሙም "አላህ ሆይ! እኔ ከወንድ ሰይጣንና ከሴት ሰይጣናት በአንተ እጠበቃለሁ።" ማለት ነው።
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ከናንተ መካከል ለጁሙዓ ሶላት የመጣ ሰው ይታጠብ።"»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"መዚይ (ስሜት በሚቀሰቀስ ወቅት የሚወጣ ፈሳሽ ነው።) የሚበዛብኝ ሰው ነበርኩ። ልጃቸው እኔ ዘንድ በመሆኗ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) (ስለብይኑ) መጠየቅ አፈርኩና ሚቅዳድ ቢን አስወድን እንዲጠይቃቸው አዘዝኩትና ጠየቃቸው። እርሳቸውም 'ብልቱን ይታጠብና ዉዱእ ያድርግ።' አሉ።" በቡኻሪ ዘገባ ደግሞ "ዉዱእ አድርግ፤ ብልትህንም እጠብ።" አሉት።
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ንፅህና የኢማን ግማሽ ነው 'አልሐምዱ ሊላህ' (ምስጋና ለአላህ የተገባ ነው) የሚለው ሚዛን ይሞላል፤ 'ሱብሐነላህ ወል'ሐምዱ ሊላህ' (አላህ ጥራት የተገባው ነው፤ ምስጋናም ሁሉ ለአላህ ነው) የሚለው በሰማያትና በምድር መካከል ያለውን ይሞላሉ ወይም ይሞላል ፤ ሰላት ብርሃን ነው፣ ምጽዋት ማስረጃ ነው፣ ትዕግስት ወገግታ (አንፀባራቂ ብርሃን) ነው፣ ቁርኣን ላንተ ወይም በአንተ ላይ ማስረጃ ነው። ሁሉም ሰው በማለዳ ወጥቶ ነፍሱን ይሸጣል። ወይ ከጥፋት ነፃ ያወጣታል ወይም ወደ ጥፋት ይጥላታል። "
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"ውሻ ከአንዳችሁ እቃ የጠጣ ጊዜ (እቃውን) ሰባት ጊዜ ይጠበው።"»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"አንዳችሁ ዉዱእ ባደረገ ጊዜ አፍንጫው ውስጥ ውሀ አድርጎ ከዚያም ያውጣው፣ በድንጋይ ያደራረቀ ሰውም (የድንጋዩን ቁጥር) ጎዶሎ ያድርገው። አንዳችሁ ከእንቅልፉ የነቃ ጊዜ እጁን ወደ ዉዱእ እቃ ውስጥ ከመክተቱ በፊት እጁን ይጠብ! አንዳችሁ እጁ የት እንዳደረች አያውቅምና።" የሙስሊም ዘገባ ላይ ደግሞ "አንዳችሁ ከእንቅልፉ የነቃ ጊዜ እጁን ሶስት ጊዜ ከማጠቡ በፊት ወደ እቃ ውስጥ አይንከረው! እርሱ እጁ የት እንዳደረች አያውቅምና።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
«ከመዲና መንገዶች በአንዱ መንገድ ላይ እርሱ ጀናባ ላይ ሆኖ ሳለ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሲያገኙት ከእይታቸው ተደብቆ በመሄድ ገላውን ታጠበ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ፈልገው አጡት። በሚመጣበት ወቅትም "አቡ ሁረይራ ሆይ! የት ነበርክ?" አሉት። እርሱም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኔን ያገኙኝ ጀናባ ላይ ሆኜ ስለነበር ገላዬን ሳልታጠብ ከርሶ ጋር መቀማመጥን ጠላሁ።" አላቸው። የአላህ መልክተኛም (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) "ሱብሓነላህ! ሙእሚን'ኮ ነጃሳ አይሆንም።" አሉት።»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"አንዳችሁ ከእንቅልፉ የነቃ ጊዜ ሶስት ጊዜ አፍንጫው ውስጥ ውሃ እየከተተ ያውጣ፤ ሸይጧን በአፍንጫው ውስጥ ያድራልና።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።