Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 5 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
"ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ እስልምናን መቀበል ፈልጌ መጣሁ። እሳቸውም በውሃና በቁርቁራ ቅጠል እንድታጠብ አዘዙኝ።"
ሶሒሕ ነው። አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና ነሳኢ ዘግበውታል።
"ውሃው ሁለት 'ቁለተይን' ከደረሰ ነጃሳን አይሸከምም።"»
ሶሒሕ ነው። አቡ ዳውድ፣ ቲርሚዚይ፣ ነሳኢይ፣ ኢብኑ ማጃህ እና አሕመድ ዘግበውታል
«ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከመፀዳጃ ቤት የወጡ ጊዜ "ጉፍራነክ" ይሉ ነበር።» (ትርጉሙም "ምህረትህን እለምንሃለሁ" ማለት ነው።)
ሶሒሕ ነው። አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።
«ወደ አላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ከተላኩ የበኒ አልሙንተፊቅ ወይም በበኒ አልሙንተፊቅ ልዑክ ውስጥ ነበርኩ። የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ዘንድ ስንደርስ በቤታቸው አላገኘናቸውም ነበር። የአማኞች እናትን ዓኢሻን አገኘን። በስጋና ዱቄት የሚሰራ (ኸዚራ) የሚባል ምግብ እንዲሰራልን አዘዘች። ለኛም ተሰራልን። በጎድጓዳ ሳህንም ተምር መጣልን። ከዚያም የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - መጥተው እንዲህ አሉን "የሚቀመስ ነገር አገኛችሁ?" ወይም "የሚቀመስ ነገር ታዘዘላችሁ?" እኛም "አዎ የአላህ መልክተኛ ሆይ!" አልን። እኛ ከአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ጋር ተቀምጠን ሳለ የርሳቸው እረኛ ፍየሎቹን ወደ ማደሪያቸው ያስገባ ጀመር። ከርሱ ጋር የምትጮህ ግልገል ነበረች። እርሳቸውም "እከሌ ሆይ! አላራባህምን?" አሉት። እርሱም "ግልገል ናት።" አላቸው። እርሳቸውም "በርሷ ቦታ አንድ ፍየል እረድልና!" አሉት። ቀጥለውም "ለናንተ ብለን የምናርድላችሁ አድርጋችሁ እንዳታስቡ። እኛ መቶ ፍየል አለን። ከመቶ እንዲጨምር ስለማንፈልግ እረኛው አንድ ሲያራባ በርሷ ቦታ አንድ እናርዳለን።" አሉ። እኔም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኔ ምላሷ ላይ ችግር ያለባት ሚስት አለችኝ። ምን ይሻለኛል?" ብዬ ጠየቅኳቸው። እርሳቸውም "እንደዛ ከሆነ ፍታት" አሉኝ። እኔም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እርሷ ከኔ ጋር የቆየ ቁርኝት አላት። ከርሷም ልጆች አሉኝ።" አልኳቸው። እርሳቸውም "ምከራት! ውስጧ መልካምነት ካለ ትታዘዝሃለች። ሚስትህን የባሪያ አመታት እንዳትመታ።" አሉኝ። እኔም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ስለ ዉዱእ ንገሩኝ።" አልኳቸው። እርሳቸውም "ዉዱእን አዳርሰህ አድርግ። በጣቶችህ መካከል ፈልፍል። ፆመኛ እስካልሆንክ ድረስም አፍንጫህ ውስጥ ውሃ ስትከት በደንብ አስገባ።" አሉኝ።»
ሶሒሕ ነው። አቡ ዳውድ፣ ቲርሚዚይ፣ ነሳኢይ እና ኢብኑ ማጃህ ዘግበውታል።
«አንድ ሰው የአላህን መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ በማለት ጠየቀ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኛ በባህር እንሳፈራለን፣ ከኛ ጋርም የተወሰነ ውሃ እንሰንቃለን። በዚህ በያዝነው ውሃ ዉዱእ ብናደርግበት እንጠማለንና በባህር ውሃ ዉዱእ እናድርግን?" የአላህ መልክተኛም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ በማለት መለሱ: "እርሱ ውሃው አፅጂ ነው፤ ውስጡ የሞተም ሐላል ነው።"»
ሶሒሕ ነው። አቡ ዳውድ፣ ቲርሚዚይ፣ ነሳኢይ፣ ኢብኑ ማጃህ እና አሕመድ ዘግበውታል