Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 28 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
«ነቢዩን ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ቃል ልንጋባ ከተወሰኑ የአንሷር ሴቶች ጋር ሆኜ መጣሁ። እንዲህም አልናቸው: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! በአላህ ላይ አንዳችንም ላናጋራ፤ ላንሰርቅ፤ ዝሙትን ላንሰራ፤ በእጆቻችንና በእግሮቻችን መካከል የምንቀጥፈውን ቅጥፈት ላንፈፅም፤ በመልካም ጉዳይም ላናምፅዎት ቃል እንጋባዎ" እርሳቸውም: "በቻላችሁት ጉዳዮችና አቅማችሁ በሚፈቅደው ጉዳዮች ቃል ተጋባኃችሁ!" አሉን። እኛም "አላህና መልክተኛው ለኛ የበለጠ አዛኝ ናቸው። የአላህ መልክተኛ ሆይ! ኑ እጅዎን ይዘርጉ ቃል እንጋባዎ።" አልን። የአላህ መልክተኛም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- "እኔ ሴቶችን አልጨብጥም። ለመቶ ሴቶች የምናገረው ቃል ለአንዲ ሴት እንደምናገረው ነው። ወይም ልክ ለአንድ ሴት እንደምናገረው ነው።" አሉ።»
ሶሒሕ ነው። ቲርሚዚይ፣ ነሳኢይ እና ኢብኑ ማጃህ ዘግበውታል
"አንድ አማኝ ወንድ አንዲትን አማኝ እንስት አይጥላ። ከርሷ አንድ ባህሪዋን ቢጠላ እንኳ ሌላ የሚወደው ባህሪ አላትና።" ወይም "ከርሱ ውጪ ያለን ባህሪ… " ብለዋል።
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"የአላህን ሴት ባሮች አትምቱ!" ዑመርም ወደ አላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - በመምጣት እንዲህ አሏቸው: "ሴቶች በባሎቻቸው ላይ እያመፁ ነው።" የዛኔም እንዲመቷቸው ፈቀዱ። የነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ሚስቶች ዘንድ በርካታ ሴቶች ስለባሎቻቸው ቅሬታቸውን አሰሙ። ነቢዩም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ አሉ: "በሙሐመድ ሚስቶች ዙሪያ በርካታ ሴቶች ስለባሎቻቸው ቅሬታ አሰምተዋል። እነዚህ ሚስቶቻቸውን የሚመቱ ባሎች ምርጦች አይደሉም።"»
ሶሒሕ ነው። አቡ ዳውድ እና ኢብኑ ማጃህ ዘግበውታል
"ከስሞቻችሁ መካከል አላህ ዘንድ ተወዳጁ ስም ዐብዱላህና ዐብዱረሕማን ናቸው።"»
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።