Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 4 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
"ዑመር ወደ ጥቁሩ ድንጋይ (ሐጀሩል አስወድ) መጣና ሳመው። እንዲህም አለ: እኔ የማትጎዳና የማትጠቅም ድንጋይ መሆንህን አውቃለሁ። እኔ ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሲስሙህ ባላይህ ኖሮ አልስምህም ነበር።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ስለ አንሷሮች እንዲህ አሉ: "አማኝ እንጂ አይወዳቸውም፤ ሙናፊቅ እንጂ አይጠላቸውም። አንሷሮችን የወደደ አላህ ይወደዋል። አንሷሮችን የጠላ አላህ ይጠላዋል።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሣቢት ቢን ቀይስን አጡት። አንድ ሰውዬ "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ስለርሱ ሁኔታ አጣርቼ አሳውቆታለሁ።" አለና ሣቢት ጋር ሲመጣ አንገቱን አቀርቅሮ ቤቱ ውስጥ ቁጭ ብሎ አገኘው። "ምን ሆነህ ነው?" አለው። ሣቢትም 'መጥፎ ነው' ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ድምፅ በላይ ድምፁን ከፍ ያደርግ ነበር። ስራውም ተበላሽቶ ከእሳት ባለቤቶች ሆኗል።" አለው። ሰውዬውም መጥቶ ሣቢት ምን እንዳለ ነገራቸው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና): " 'ወደርሱ ሂድና አንተ ከእሳት ሰዎች ሳትሆን ከጀነት ሰዎች ነህ በለው።' አሉት ሰውየውም ታላቅ የብስራት ዜና ይዞ በድጋሚ (ወደ ሣቢት) ተመለሰ።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ከናንተ ምርጡ እኔ ያለሁበት (ዘመን) ትውልድ ነው። ከዚያም ከነርሱ በኋላ ቀጥለው የሚመጡት፤ ከዚያም ከነርሱ ቀጥለው የሚመጡት ናቸው።" ዒምራንም እንዲህ አለ: "ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ከሳቸው ትውልድ በኋላ ሁለት ትውልዶችን ይጥቀሱ ወይም ሶስት አላውቅም።" ከዚያም ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ አሉ: "የሚከዱ የማይታመኑ፤ ምስክርነት ሳይጠየቁ የሚመሰክሩ፤ ስለትን ተስለው ስለታቸውን የማይሞሉ፤ በነርሱ ላይ ደንዳና ሰውነት የሚስተዋልባቸው ሰዎች ከናንተ በኋላ ይመጣሉ።"»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።